gera doctor

የሆድ  ድርቀት (Constipation) ምንድን ነው?

የሆድ ድርቀት በሚፈለገው እና በሚጠበቀው ልክ የሰገራ አለመውጣት እና ለመውጣትም መቸገር ሲሆን ብዙውን ጊዜ ጥቂት፣ ጠንካራና ደረቅ ሰገራ እና ማስማጥ መለያዎቹ ናቸው። አንድ ሰው በሳምንት ውስጥ ከ3 ላነሰ ጊዜ ሰገራ ከወጣ የሆድ ድርቀት አለበት ልንል አንችላለን።

ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው?

  1. በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ፤
  2. ዝቅተንኛ የፋይበር መጠን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር፤
  3. የአካል ብቃት አንቅስቃሴ አለማድረግ፤
  4.  ሰአቱን ጠብቆ ሽንት ቤት አለመሄድና ሽንት ቤት የመጠቀም ስሜት በመጣበት ሰአት አለመጠቀም፤
  5. የተለያዩ የደም ግፊት፣ የድባቴ፣ የህመም ማስታገሻ፣ የጨጓራ አንታሲድ መድሀኒቶች (አንደ ጎንዮሽ ተጽእኖ) ለድርቀት ሊያጋልጡ ይችላሉ።
  6. አንድ አንድ የአንጀት አና ሌሎች ሕመሞች የሆድ ድርቀትን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

የሆድ ድርቀት መከላከያ መንገዶቹና መፍትሔው

1. ሽንት ቤት የመጠቀም ስሜት በመጣበት ሰአት ወዲያውኑ መጠቀም፤

2. ሰአቱን ጠብቆ ሽንት ቤት የመሄድ ልምድን ማዳበር፤ ለምሳሌ ቁርስ ከተመገቡ ከ 20 ደቂቃ በኋላ ሽንት ቤት መጠቀም።

3. በቂ ፈሳሽ (ውሃ) መውሰድ። በቀን አስከ 2 ሊትር ውሃን መጠጣት። በየምግብ ሰአቱ 2-3 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት።  

4. በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን መውሰድ (አትክልትና ፍራፍሬ፣ አረንጓዴ ጎመን፣ እንደ ባቄላና አተር ያሉ ጥራጥሬወችን)

5. አይብን መቀነስ (አይብ ለሆድ ድርቀት ያጋልጣል)።

6. አልኮል፣ ቡና አና ሻይን መቀነስ፤

7. ምግብ ከመመገብወ በፊት ለብ ያለ ወይም ቀዝቃዛ ውሃን በመጠጣት የአንጀት አንቅስቃሴን ማነቃቃት፤

8. ጣፋጭ ምግቦችን መቀነስ (ጣፋጭ ምግቦች የአንጀት ባክቴሪያወችን በማብዛት ትልቁ አንጀት ከሰገራ ይልቅ በፈስ እንዲጨናነቅ ያደርጋሉ)።

9. በቂ የአካል ብቃት አንቅስቃሴን ማድረግ (በቀን ለ20/30 ደቂቃ መጓዝ የአንጀት እንቅስቃሴን ይጨምራል)።

10. በሃኪም ያልታዘዘ መድሃኒትን አለመውሰድ።

 

ከድርቀት በተጨማሪ የሚከተሉት ምልክቶችን ካዩ ወዲያውኑ ወደ ጌራ ሐኪሞች ይደውሉ (0988151617)።

1. ከላይ የተዘረዘሩትን መከላከያ መንገዶችም አድርገው ድርቀቱ ካልተሻሻለ፣

2. አንዴ ድርቀት አንዴ ደግሞ ተቅማጥ የሚያስቸግርወት ከሆነ፣

3. ከሰገራ ጋር ደም ካዩ፣

4. ከድርቀቱ በተጨማሪ ትኩሳትና ከባድ የሆድ ህማም ካለብወት።

Why Choose Gera Home Care ?

Time Efficiency

Minimize downtime and optimize consultation times for busy professionals.

Customized Care Plans

Tailored healthcare plans that address each patient’s individual needs.

Workplace Wellness Initiatives

Programs designed to foster healthier, more productive work environments.

Cost Savings

Reduce healthcare costs for employees and organizations alike.

WhatsApp
Telegram
TikTok
Scroll to Top